ፀሐይ ለቤተሰብ የወላጅነት ት/ቤት
የልጆችዎን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ የሚረዱ ትምህርቶችን ከባለሞያዎች አሁኑኑ ያግኙ!
የልጆችዎን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ የሚረዱ ትምህርቶችን ከባለሞያዎች አሁኑኑ ያግኙ!
ብዙ ሰዎች በራስ መተማመን በተፈጥሮ የተሰጠ ፀጋ ነው ብለው ያስባሉ፣ ግን አይደለም፡፡ በራስ መተማመን ያለማቋረጥ የሚያድግ ክህሎት ነው። ያለማቋረጥ ስንል ያለማቋረጥ መሞከር፣ ያለማቋረጥ መውደቅ፣ ያለማቋረጥ መነሳት፣ ያለማቋረጥ መማር ማለት ነው። በራስ መተማመን ልዩ የሚያደርገው ሁሉንም ሰው ከሚያመሳስለው ነገር መጀመሩ ነው።
ሁሉም ሰው አንዳንዴ ይናደዳል! ቁጣ ለሰው ልጅ ራስን ለመጠበቅ እና ለመከላከል ወሳኝ ውስጣዊ ስሜት ነው፤ ገንቢ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ሲውል ሰዎች እራሳቸውን እና ሌሎችን ለመጠበቅ እና ኢፍትሃዊነትን ለመቋቋም ጥንካሬ እና ድፍረት እንዲያገኙ ይረዳቸዋል።
የሰው ልጅ ስሜታዊ እና ማኅበራዊ እድገት አንዳንድ ጊዜ ከአዕምሯዊ ዕዉቀት የበለጠ አስፈላጊ የሚሆንበት ግዜ አለ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማኅበራዊ እና ስሜታዊ ትምህርትን አንድ ጊዜ ተምረው በዕለት ተዕለት ስራቸው ላይ የሚተገበሩ ተማሪዎች፣ ምንም ዓይነት የማኅበራዊ እና የስሜታዊ ትምህርትን ካልወሰዱ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያሳያሉ።
ጤናማ ግንኙነት የሚመሠረተዉ እንዴት ነው? ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረንስ ዕድለኞች መሆን አለብን? በጭራሽ! ግንኙነትን የመገንባት ክህሎት በጊዜ ሂደት የሚማሩት እና ተግባራዊ የሚያደርጉት ነገር ሲሆን፣ ጠንካራ ግንኙነትን መመስረትን ከሁለቱም ወገን ትጋትን እና የማያቋርጥ ጥረት ማድረግን ይፈልጋል።
በዚህ ትምህርት ውስጥ ተሳታፊዎች በስሜት ቁስል እና በማገገም ሂደት መካከል ያለውን ውስብስብ መስተጋብር በጥልቀት ይረዳሉ። ስለ ፈውስ ሂደት ስነ-ልቦናዊ፣ ስሜታዊ እና አካላዊ ተፅዕኖዎች ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ያገኛሉ። አሳታፊ በሆነ አቀራረብ፣ አቅምን የሚያበረታቱ በማስረጃ የተመሰረቱ ልምምዶችን እና ራስን የመንከባከብ ስልቶችን እንቃኛለን።
ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ እ.ኤ.አ በ 2005 የተቋቋመ ሀገር በቀል ሶሻል ኢንተርፕራይዝ ሲሆን የልጆች፣ የታዳጊዎችን እና የወጣቶችን ህይወት ለማሻሻል ይሰራል። ዊዝ ኪድስ ዘላቂ የሆነ የባህሪ እና ማህበረሰባዊ ለውጦች ለማምጣት እድሜን፣ ቋንቋን፣ ባህልን እና የእድገት ደረጃን ያማከሉ በጥናት የተደገፉ የፈጠራ ስራዎችን ቴሌቪዥን፣ ራዲዮን እና በይነ መረብ/ኢንተርኔት፣ ት/ቤቶችን፣ ፌስቲቫሎች እና ማህበረሰባዊ ስብሰባዎችን ተጠቅሞ በማሰራጨት ከ 10 ሚሊየን በላይ ህፃናትን፣ ታዳጊዎችን እና ቤተሠቦቻቸውን እያገለገለ ይገኛል። ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ ለሀገር እያደረገ ባለው መልካም አስተዋጽኦ በርካታ አለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን በሁሉም የእድሜ ክልል ላይ ላሉ ህፃናት/ልጆችን እና ወጣቶችን ለመደገፍ ፀሐይ ለቤተሰብ፣ ፀሐይ መማር ትወዳለች፣ የጥበብ ልጆች እና ወጣት ፈጣሪዎች /ተመራማሪዎች የሚሉትን አራት የፈጠራ ስራዎች /ኢኖቬሽኖች ይጠቀማል።