ስነ-ልቦና
በፅናት ከስሜት እና ከአዕምሮ ቁስለት የማገገም ጉዞ
በስሜት ቁስል እና በማገገም መካከል ያለውን ውስብስብ ትስስር በመረዳት፣ ስለ ፈውስ ሂደት ስነ-ልቦናዊ፣ ስሜታዊ እና አካላዊ ተፅዕኖዎች ጠቃሚ ግንዛቤዎችን አዳብሪ፣ አቅም የሚሰጡ፣ በማስረጃ የተመሰረቱ ልምምዶችን እና ራስሽን የመንከባከብ ስልቶችን ከእኛጋር አብረሽ ተለማመጂ።
የዚህ ፕሮግራም አባል ስትሆኝ የምታገኛቸው ዋና ዋና ጥቅሞች፡
ከአዕምሮ ቁስል ማገገም
- የአዕምሮ ቁስል ምንነት እና ተጽዕኖዎች ላይ ጥልቅ ግንዛቤን ታገኛለሽ።
- የአዕምሮ ቁስለት እንዴት እንደሚከሰት እና ምልክቶቹ ምን እንደሆኑ ትረጂያለሽ።
- የአዕምሮ ቁስልን ለመፈወስ እና ለመንከባከብ የተዘጋጁ ተግባራዊ ስልቶችን ትማሪያለሽ።
- የአዕምሮ ቁስል አካላዊ እና ስሜታዊ ተጽዕኖዎችን መለየት ትችያለሽ።
ራስን መንከባከብ እና ይቅር
- ለራስሽ ይቅርታን እንዴት ማዳበር እንደምትችይ ትማሪያለሽ።
- ራስሽን ለመንከባከብ ተግባራዊ ዘዴዎችን ትለማመጃለሽ።
- በራስሽ እንክብካቤ ወቅት የሚከሰቱ ስሜታዊ እንቅፋቶችን መለየት እና ማስተካከል ትችያለሽ።
- የተረጋጋ እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ትገነቢያለሽ።
ስሜትን መረዳት እና መግለጽ
- ስሜትሽን በምልክት፣ በሰውነት ቅኝት እና በቀለም መወከልን ትማሪያለሽ።
- የስሜት ቁስል ሲፈጠር የአዕምሮሽን ምላሽን ትረጂያለሽ።
- የማስተዋልን ጥቅም እና ስሜትሽን የመቆጣጠር ችሎታሽን ታዳብሪያለሽ።
- ከራስሽ እና ከሌሎች ጋር የተሻለ ግንኙነትን ትፈጥሪያለሽ።
የማሰላሰያ እና የጥሞና ጊዜን ማወቅ
- የማሰላሰያ እና የጥሞና ጊዜን በመጠቀም የአዕምሮ ሰላምሽን ታገኛለሽ።
- ጭንቀትን የሚቀንሱ እና ትኩረትሽን የሚጨምሩ ቴክኒኮችን ትለማመጃለሽ።
- ሰውነትሽን በመቃኘት እና በንቃት በመኖር የአዕምሮ እና የአካል ጤናሽን ታሻሽያለሽ።
- የተረጋጋ እና ሚዛናዊ ሕይወትን ትገነቢያለሽ።