እንኳን ደህና መጣሽ!
የለውጥ ጉዞሽ እዚህ ይጀምራል፤ 

Write your awesome label here.

ብቃትሽን ለማሻሻል ትክክለኛውን እርምጃ ወስደሻል!

ብቁ እና ተፈላጊ የህፃናት ባለሙያ ለመሆን የሚያስፈልግሽን ሁሉ እዚህ ድህረገጽ ላይ ታገኛለሽ።
✅ በራስ መተማመንሽን የሚገነባ ስልጠና
✅ ወላጅነትሽ ላይ ባለሽ ብቃት እና ክህሎት በራስሽ የምትኮሪበት
✅ ለስራ ዝግጁ የሚያደርግሽ ሞያዊ እውቀት


ከግምት ወደ በራስመተማመን ያለው ወላጅነት!

በዘልማድ ከመመራት ወጥተሽ፣ በሳይንስ የምትመራ ባለሙያ ወደመሆን ትሸጋገሪያለሽ። ይህም

✅ከመጭንቀት →ወደ መረጋጋት እና ደህንነት
✅ከመገመት → ወደ እርግጠኛነት እና ትክክለኛ
✅መንገድ ከተስፋ → በስልጠና ወደ ሚገኝ አስተማማኝ ብቃት

መሰረታዊ የህጻናት እንክብካቤ

ለልጆች እድገት ወሳኝ የሆነውን መሰረታዊ የህጻናት እንክብካቤ ራሳችንን በማስተማር ልናዳብረው የምንችለው ወሳኝ ክህሎት እንደሆነ ታውቃላችሁ? መሰረታዊ የህጻናት እንክብካቤ ማለት ምን ማለት ነው? እንዴት ይዳብራል? እነዚህን ጥያቄዎች ለራሳችሁ መመለስ ከፈለጋችሁ እንዲሁም የሚከተሉትን ነገሮች ማግኘት ካሻችሁ መሰረታዊ የህጻናት እንክብካቤ ፕሮግራምን አሁኑኑ ተቀላቀሉ!

ህፃናትን መረዳት 

  • የህፃናትን የስሜት ደረጃዎች በጥልቀት መገንዘብ ያስችላችኋል፡፡
  • በየእድሜያቸው ልጆችን ለመረዳት የሚያስችሉ ተግባራዊ ስልቶችን ማወቅ፡፡ 
  • የእድገት ምዕራፎችን መለየት እና የእድገት መዘገት ሲኖር ቀድሞ በመለየት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ፡፡

ምላሽ ሰጪ እንክብካቤ

  • ጠንካራ ትስስርን መፍጠር ትችላላችሁ፡
  • ስሜታዊና ማህበራዊ እድገትን መገንባት ትችላላችሁ፡፡
  • የዕለት ተዕለት የህጻናት እንክብካቤ ችሎታዎችን ማጠናከር ትችላላችሁ፡፡

የአመጋገብና የመመገብ ልማዶች 

  • የልጃችሁን የአመጋገብ ዘይቤ ምን አይነት እንደሆነ መረዳት፡፡
  • የቤታችሁን የአመጋገብ ዘይቤ እንዴት ማስተካከል እንደምትችሉ መገንዘብ ትችላላችሁ፡፡
  • አመጋገብ ከሕይወት ዘመናችን ጋር እንዴት ሊገናኝ እንደሚችል ታውቃላችሁ፡፡ 

ሥነ ምግባር እና የማህበራዊ 

  • በሥነ ምግባር አማካኝነት ሊፈጠሩ የሚችሉ ቁርኝቶችን ማዳበር ትችላላችሁ።
  • ግንኙነቶችን የሚያጠናክሩ ስልቶችን ማወቅ ትችላላችሁ።
  • በስሜት ጠንካራ የሆነ እና ሥነ ምግባር ያለው ልጅ ማሳደግ እንዴት እንደሆነ ትማራላችሁ።

አጠቃላይ ደህንነት እና ጥበቃ

  • ተግባራዊ የደህንነት መጠበቂያዎችን ማወቅ።
  • ለአደጋ ጊዜ ዝግጁ መሆን።
  • የተንከባካቢዎችን እርዳታ ማግኘት።

ቅድመ ማነቃቃት

  • የህፃናትን አዕምሮ ለማበልጸግ በጨዋታ እያዋዛችሁ ማገዝን ትለማመዳላችሁ/ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
  • የህፃናት ልጆችን አዕምሮ እድምያቸው ባማከለ መልኩ ለማሳደግ ተግባራዊ የሆኑ መሣሪያዎችን በቀላሉ በማግኘት መጠቀም ትችላላችሁ፡፡
  • በራስ መተማመን ያላችሁ በመሆን ከልጃችሁ ጋር ጥሩ ቁርኝት እንዲኖራችሁ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ 

ንጽሕና እና ጤንነት

  • እያንዳንዱ ልጅ ሊኖረው የሚገባውን የጤና ሁኔታ ማወቅ ትችላላችሁ፡፡
  • ቤታችሁን የልጃችሁ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
  • የዕለት ተዕለት ልማዶችን ጤናማ ማድረግ ትማራላችሁ፡፡ 

ጭንቀትን መቆጣጠሪያ እና ደህንነትን መጠበቂያ-ለእንክብካቤ ሰጪዎች 

  • ድካም ሲሰማችሁ ማወቅ እና መረዳት መቻል ትጀምራላችሁ።
  • እራሳችሁን የምትንከባከቡበትን መንገዶች ማወቅ ትችላላችሁ።
  • ሊያግዟችሁ የሚችሉ አጋሮችን ማፈላለግ እንዳለባችሁ ትረዳላችሁ፡፡  

በጨዋታ ላይ የተመሠረተ ትምህርት

  • ለአስተሳሰብ እድገት ድጋፍ ማድረግ መቻል፡፡
  • የማህበራዊ እና ስሜታዊ ክህሎቶችን ማሻሻል ትችላላችሁ፡፡ 
  • የየአካል እና የጤና ቅንጅትን ማሳደግ ትጀምራላችሁ፡፡  

በህጻናት እንክብካቤ ባለሞያ መሆንን

  • የሞያዊ እድገት ክህሎትን ማወቅ፡፡
  • የቃለ መጠይቅ ችሎታ እና የደመወዝ ስምምነት ላይ በራስ መተማመንን ማዳበር፡፡ 
  • ሞያዊ እድገት 

ደረጃ በደረጃ የሚገነባ ክህሎት!

በነዚህ አስር ተግባራዊ ትምህርቶች ስታልፊ እውቀትን በተግባር በመለማመድ የወላጅነት ብቃትን እያዳበርሽ ትሄጃለሽ።

➊ሞጁል 1: የልጆችን እድገት መረዳት

የልጆችን ባህሪ እና የአእምሮ እድገት በሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እንድትረጂ እና ግራ መጋባትን ወደ ልበ-ሙሉነት እንክብካቤ ትተክያለሽ።

➋ሞጁል 2፡ምላሽ ሰጪ እንክብካቤ

ከልጆች ጋር ጠንካራ ስሜታዊ ትስስር በመፍጠር፣ የእንክብካቤ ጊዜሽን ቀላል እና ትርጉም ያለው ታደርጊያለሽ።

➌ሞጁል 3:ቅድመ ማነቃቂያ

የልጆችን የአእምሮ ብቃት ገና በትንሽ እንድሜያቸው ጀምሮ ለማንቃት የሚያስችሉ ተግባራዊ ዘዴዎችን ትቀስሚያለሽ።

➍ሞጁል 4:ንጽህናና ጤና

ልጆችን ከበሽታ በመጠበቅ ረገድ ያለሽን ስጋት የሚያስወግድ እና ንቁ እንድትሆኚ የሚያደርግ ሙያዊ እውቀት ታገኛለሽ።

➎ሞጁል 5: አመጋገብና ስርዓተ-ምግብ

እያደገ ላለ አካል ምን እንደሚያስፈልገው በትክክል በማወቅ፣ ጤናማ ትውልድ የመገንባት አቅም ይኖርሻል።

➏ሞጁል 6: አዎንታዊ ስነ-ምግባር እና ስሜታዊ ብቃት (SEL)

ያለ ጩኸትና ቅጣት የልጆችን ባህሪ በረጋ መንፈስ የመምራት እና ስሜትን የመቆጣጠር ጥበብን ትላበሻለሽ።
Write your awesome label here.

➐ሞጁል 7: ደህንነትና ጥበቃ

አደጋን አስቀድሞ የመከላከል ብቃትሽ በመጨመር ልልጆችሽ አስተማማኝ ከለላ ላንቺ ደግሞ የአእምሮ እረፍት ታገኛለሽ።

➑ሞጁል 8: የአሳዳጊዎች ስነ-ልቦናዊ ደህንነት

ራስሽን ከውጥረት በመጠበቅ ለልጆችሽ የተሻለች እና ሁሌም ዝግጁ የሆንሽ ተንከባካቢ/ባለሙያ ትሆኚያለሽ።
Write your awesome label here.

➒ሞጁል 9:በጨዋታ መማር/ጨዋታን ያማከለ ትምህርት

Write your awesome label here.
እያንዳንዱን የጨዋታ ጊዜ ወደ ትልቅ የመማሪያ እና የክህሎት ማዳበሪያ አጋጣሚ የመቀየር ዘዴን ትማሪያለሽ።

➓ሞጁል 10: ሙያዊነትና የሥራ ዝግጁነት

ያገኘሽውን ጥልቅ እውቀት እና ክህሎት ወደ ተከበረ፣ ተፈላጊ እና ገቢ የሚያስገኝ የሙያ መስመር እንድትቀይሪ ያግዝሻል/ትቀይሪያለሽ።
👉 🎓 ስልጠናውን ስታጠናቅቂ ብቃት ያላት ባለሞያ እና ለስራ ዝግጁ ነሽ!

Write your awesome label here.

በምታደርጊው ጉዞ ብቻሽን አይደለሽም!

አዎ በምታደርጊው ጉዞ በዘርፉ ካሉ ባለሙያዎች ጋር የምትመካከሪበት እና ከሌሎች እናቶች ጋር ልምድ የምትለዋወጪበት ጠንካራ ቤተሰብ ይጠብቅሻል።

✅ለጥያቄዎችሽ ፈጣንና ሳይንሳዊ ምላሽ የሚሰጡ ባለሙያዎች።

✅ተሞክሯቸው የሚያጋሩሽ በርከት ያሉ ትጉህ ወላጆች
✅ብቃትሽን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት
✅በፈለግሽው ሰዓት እና ቦታ ሆነሽ የምታገኝው ትምህርትና ድጋፍ